ሁለትዮሽ ግንኙነቶች
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶችና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መካከል ያለው የሁለትዮሽ ግንኙነት፣ እ.ኤ.አ. በ1973 መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከተመሠረተ ወዲህ በዘላቂ ወዳጅነትና በጋራ ጥቅም ላይ የተገነባ የትብብር ምሳሌ ነው። ባለፉት ዓመታት ግንኙነቱ በተለያዩ ዘርፎች፣ በተለይም በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በባህል መስኮች፣ በጋራ ከፍተኛ ደረጃ ጉብኝቶችና ይፋዊ ልውውጦች እየተመራ ጉልህ እመርታ አሳይቷል። ከእነዚህም ዋነኛው የተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ክቡር ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን (አላህ ይጠብቃቸው) እ.ኤ.አ. በኦገስት 2023 ወደ ኢትዮጵያ ያደረጉት ይፋዊ ጉብኝት ሲሆን፣ በጉብኝታቸው ወቅት ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችሉ መንገዶችን በማስመልከት ተነጋግረዋል።
ይህንኑ መነቃቃት መሠረት በማድረግ፣ ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ሼክ ሻክቡት ቢን ናህያን አል ናህያን እ.ኤ.አ. በጃንዋሪ 2026 የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስን ጨምሮ ከከፍተኛ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል። ውይይታቸው የሁለትዮሽ ትብብርን በማጠናከር፣ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን በማራመድ፣ ሰብአዊ ሁኔታዎችን በመመልከትና በአፍሪካ ቀንድና በሱዳን የሰላምና የመረጋጋት ጥረቶችን በመደገፍ ላይ ያተኮረ ነበር። በመቀጠልም በዚያው ዓመት በማርች ወር የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ይፋዊ ጉብኝት አድርገው፣ ከኤምሬቶች ፕሬዝዳንት ክቡር ሼክ መሐመድ ቢን ዛይድ አል ናህያን (አላህ ይጠብቃቸው) ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነቱን የበለጠ ለማስፋትና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ተገናኝተዋል።

የኢኮኖሚ ትብብር
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶችና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መካከል ያለው ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት በንግድና በኢንቨስትመንት ዘርፎች የተረጋጋ ዕድገት ማሳየቱን ቀጥሏል። በሁለቱ ሀገራት መካከል የነዳጅ ያልሆነ ንግድ እ.ኤ.አ. በ2025 ወደ 6.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ደርሷል፤ ይህም በ2024 ከነበረው 1.4 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር እና በ2023 ከነበረው 834 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ከፍ ያለ ነው። ኤምሬቶች ከኢትዮጵያ ጠቅላላ የዓረብ ዓለም ንግድ ወደ 40 በመቶ የሚሆነውን በመሸፈን የኢትዮጵያ ቀዳሚ የዓረብ የንግድ አጋር ናት።
የሁለትዮሽ ኢኮኖሚያዊ ትብብር ሎጂስቲክስን፣ ወደቦችን፣ ፋይናንስን፣ ግብርናንና ቴክኖሎጂን ጨምሮ ቁልፍ ዘርፎችን ያካትታል። ይህ ትብብር በኤዲ ፖርትስ ግሩፕና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እንዲሁም በዲፒ ወርልድና በኢትዮጵያ ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር መካከል የተደረጉትን ስምምነቶች ጨምሮ በዋና ዋና ስትራቴጂካዊ አጋርነቶች ላይ የተመሠረተ ነው። የጋራ ተነሳሽነቶቹ በኦሞላት ሴኪዩሪቲ ፕሪንቲንግ (Oumolat Security Printing) እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መካከል የገንዘብ ኅትመትና የጉምሩክ መፍትሔዎችን፣ በኢትሃድ ክሬዲት ኢንሹራንስና በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መካከል የፋይናንስ አገልግሎቶች ትብብርን፣ እንዲሁም ከአል ዳህራ ሆልዲንግ ጋር የግብርና ኢንቨስትመንቶችን ያካትታሉ።
እነዚህን የንግድ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከርና ለንግዱ ማኅበረሰብ አዳዲስ ዕድሎችን ለመፍጠር፣ የዱባይ-ኢትዮጵያ ቢዝነስ ኮኔክት (Dubai–Ethiopia Business Connect) ዓውደ ርዕይ እ.ኤ.አ. በሜይ 2026 በአዲስ አበባ ተካሂዷል። ዓውደ ርዕዩ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ምክር ቤትና ከዱባይ ቻምበርስ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ሲሆን፣ 530 የሁለትዮሽ የንግድ ስብሰባዎችን አመቻችቷል። የኢትሃድ አየር መንገድ በቀጥታ የሚያደርጋቸውን በረራዎች ጨምሮ የተጠናከረው የአየር ትስስር ጉዞንና የንግድ ልውውጥን ማቀላጠፉን፣ የንግድ ፍሰትን ማሳደጉንና የጋራ የኢንቨስትመንት ጥረቶችን መደገፉን ቀጥሏል።

የባህል ትብብር
በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶችና በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መካከል ያለው ትብብር በዕውቀት ሽግግር፣ በአቅም ግንባታና በወጣቶች ማብቃት ላይ በሚያተኩሩ የጋራ ተነሳሽነቶች እንዲሁም በሁለቱ ሕዝቦች መካከል ያለውን ትስስር በሚያጠናክሩ ሰብአዊ ጥረቶች አማካኝነት ወደ ባህል፣ ትምህርትና ማኅበራዊ መስኮች ተስፋፍቷል።
እ.ኤ.አ. ጁላይ 23 ቀን 2024 በአዲስ አበባ የመንግሥት ዘመናዊነትና የልምድ ልውውጥ ማዕቀፍ ሥር "5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች" ተነሳሽነት ተጀምሯል። ተነሳሽነቱ የኢትዮጵያ ወጣቶችን በዲጂታልና በፕሮግራሚንግ ክህሎቶች በማስታጠቅ፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ ተሳትፎአቸውን ለማሳደግና በኮዲንግና በሰው ሠራሽ አስተውሎት (አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ) ዘርፍ ካሉ ለውጦች ጋር እኩል እንዲራመዱ ለማድረግ ያለመ ነው። በተጨማሪም በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ የዛይድ በጎ አድራጎት ሩጫ በሁለቱ ሀገራት ከፍተኛ ባለሥልጣናት በተገኙበት ተካሂዷል፤ በዚህም ወቅት ለኢትዮጵያ የሕፃናት ልብ ሕክምና ሆስፒታሎች 300,000 የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ይፋ ተደርጓል።
ከዚህም ባሻገር እ.ኤ.አ. ከጁን 25 እስከ 26 ቀን 2026 አዲስ አበባ የ"ሂሊ" ክልላዊ ጉባኤን አስተናግዳለች፤ ጉባኤው በአንዋር ጋርጋሽ ዲፕሎማሲያዊ አካዳሚ አዘጋጅነት ከኤምሬትስ የስትራቴጂክ ጥናትና ምርምር ማዕከል (ECSSR) እና ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት (IFA) ጋር በመተባበር የተካሄደ ነው። "የኤምሬቶች–አፍሪካ አጋርነትን ለዘላቂ ኢኮኖሚያዊ ልማት ማጠናከር" በሚል መሪ ሃሳብ የተካሄደው ይህ መድረክ፣ ባለሥልጣናትን፣ ፖሊሲ አውጪዎችንና የመንግሥትና የግል ዘርፍ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ በንግድ፣ በኢንቨስትመንት፣ በአየር ንብረት ደኅንነት፣ በወሳኝ ማዕድናትና በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ጨምሮ በቁልፍ ጉዳዮች ላይ ተወያይቷል።